ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

ቤንዚን – 47 ነጥብ 83 በሊትር

ነጭ ናፍጣ – 49 ነጥብ 02 በሊትር

ኬሮሲን – 49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ – 53 ነጥብ 10 በሊትር

ከባድ ጥቁር ናፍጣ – 52 ነጥብ 37 በሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ – 98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውቋል፡፡