የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺሕ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያደረገ መሆኑን ገለጸ

ሰኔ 29/2014(ዋልታ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺሕ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ።

የድርጅቱን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜናዊ አፋር ኮኔባ አካባቢ ዛሬ መድረሳቸውን እና ወደ መጋዘን እየተራገፈ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።

በየስድስት ሳምንት ልዩነት “በአፋር ክልል በግጭትና በድርቅ ምክንያት” ለተፈናቀሉ ከ650 ሺሕ በላይ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ጠቁሟል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት በክልሉ ለ80 ሺሕ ዜጎች የሚሆን የምግብ እርዳታ ማድረሱን ጠቁሞ አሁንም የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጿል።