ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ከፀጥታ አካላት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

ሐምሌ 1/2014 (ዋልታ) ሕዝበ ሙስሊሙ 1 ሺሕ 443ኛው ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲከበር ከፀጥታና ደኅንነት አካላት ጎን እንዲቆም የፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 1 ሺሕ 443ኛው ዒድ አል አድሃ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በመልዕክቱ የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኃይል እና ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ሕዝበ ሙስሊሙ ከፀጥታና ደኅንነት አካላት ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል፡፡