በአየር ፀባይ ምክንያት ተቋርጠው ከነበሩት በረራዎች አብዛኛዎቹ መጀመራቸው ተገለጸ

ሐምሌ 4/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱንም ገልጿል።

በተያያዘ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች በአብዛኛው መጀመራቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ተጨማሪ መረጃዎች ማድረሱን እንደሚቀጥልም አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW