50 ሺሕ 337 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ መመለሳቸው ተገለጸ

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) ከሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በመመለስ ሂደት እስካሁን 50 ሺሕ 337 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

ለሦስት ወራት ከ15 ቀናት በተደረገ ዜጎችን የመመለስ ሥራም በ137 በረራዎች 50 ሺሕ 337 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተመላክቷል፡፡

ከተመላሾች ውስጥ 37 ሺሕ 485 ወንዶች፣ 9 ሺሕ 225 ሴቶች እና 3 ሺሕ 628 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እና ህፃናት መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ሥራ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW