በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ የሕዝብ ተሳትፎና የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ ይፈጸማል ተባለ

ጃንጥራር ዓባይ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ሂደት የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

ኃላፊው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሐምሌ 01 ቀን 2014 እጣ አወጣጥ ላይ የተገኘውን ግኝት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ የወሰደው ፈጣን እርምጃ ፍትሕን ከማስፈን አኳያ ተገቢነት ያለው ውሳኔ ነው፡፡

የማጣራት ሥራው በሚመለከታቸው ተቋማት እና ከፍተኛ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የተከናወነ ሥራ መሆኑም የግኝቶቹን ተአማኒነት ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ለሚከናወኑ የእጣ አወጣጥ ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባ ገልጸው ለተግባራዊነቱም እንተጋለን ብለዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW