“ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፎቶ አውደ ርዕይ በጅማ ተከፈተ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ስድስተኛው “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

አውደ ርዕዩና የፓናል ውይይቱ “ብሩህ ሀሳብ፣ ሥራ እና ክህሎት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በመድረኩ ላይ የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የኢትዮጵያ እናቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በተያዘው መርኃ ግብር መሰረት የዝግጅቱ ተሳታፊዎች የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

የእለቱ የፎቶ አውደ ርዕይ በሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፣ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ እና በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮች ተከፍ ተከፍቷል፡፡

በ12 ከተሞች የሚዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩና የፓናል ውይይቱ በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ደምሰው በነበሩ (ከጅማ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!