የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ በጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በከተማ አስተዳደሩ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ዘገባ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በ2015 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የበጀት እና ሌሎች ልዩ ልዩ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW