1ሺሕ 166 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺሕ 166 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 14 ሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡