ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በ2015 የተልዕኮውን 60 በመቶ እንደሚፈጽም አስታወቀ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በ2015 በጀት ዓመት 60 በመቶ ተልዕኮውን እንደሚፈጽም አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ላይ የ2015 በጀት ገቢራዊ እቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተባባሪና አማካሪ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀው የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው በትግበራ ምዕራፍ 20 ሺሕ መድረኮች በማዘጋጀት ሁለት ሚሊየን ሰዎች እናወያያለን ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ3 ነጥብ 2 ቢለየን በላይ ብር ከመንግሥት የሚጠይቅ ሲሆን 208 ሚሊየን ብሩ ከአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡

አጀንዳ እና ተሳታፊ ልየታ፣ መዋቅር ዝርጋታና መሰል ተግባራት የቀጣይ ተግባራት አቅጣጫዎች መሆናቸውም ተገልጿል ሲል የዘገበው ኤፍቢሲ ነው፡፡