የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ በትብብር እንሠራለን – በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) ከጦርነት ቀጠናዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ በትብብር እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ገልጹ።

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ ጋር ተወያይተዋል።

ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ከጦርነት ቀጠናዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ የጎንደር አካባቢ ሕዝብ የሚያደርገውን ርብርብም አድንቀዋል።

ተፈናቃዮችን ወደቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ በትብብር እንደሚሠሩም ገልጸው በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው የቀደመ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በበኩላቸው ውይይቱ ተፈናቃዮችን ከመደገፍ በተጨማሪ በአሜሪካ ከተሞችና በጎንደር ከተማ መካከል ያለውን እህትማማችነት ለማጠናከር በር ከፋች እንደነበር መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።