የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ዛሬ ይጫወታል

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ዋሊያዎቹ)  በቻን ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ዛሬ ይጫወታል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያ 0 ለ 0 መለያየታቸው ይታወሳል።

የዋሊያዎቹ ዋና አሰጣኝ ውበቱ አባተ ለጨዋታው ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ በታንዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲዬም ነው የሚደረገው፡፡