በአትሌቲክሱ የተገኘው ድል የኢትዮጵያዊያንን አንድነት የበለጠ ያጠናክረ ታሪካዊ ድል ነው- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበውን አኩሪ ድል በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በሻምፒዮናው የተመዘገበውን ድል አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ድሉ በተለይም በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያዊያንን አንድነት የበለጠ ያጠናከረ በመሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል።

ድሉ በህብረት፣ በመተጋገዝና በመተባበር ከተሰራ በአስቸጋሪ ወቅትም ቢሆን ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ያመላክት ነው ብለዋል።

በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበው አኩሪ ድልም በሌሎች ተግባራት ላይ ለመድገም መነሳሳታን የሚፈጥር በመሆኑ መላው የክልሉ ነዋሪ ብሎም አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሪቱ እየተከናወኑ በሚገኙ የሰላምና የልማት ስራዎች በትብብር፣ በመተጋገዝና በመደጋገፍ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

ለተገኘው ውጤትም ጀግኖች አትሌቶችን፣ አሰልጣኞችንና መላው የልዑካን በድኑ አባላትን በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም አመስግነው ለመላው ኢትዮጵያውያንም በተገኘው አኩሪና ታሪካዊ ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW