ኢትዮ ቴሌኮም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ 70 ቢሊዮን ብር ለማስገባት ታቅዶ የእቅዱን 87 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ የተስተዋሉ አለመረጋጋቶች ለቴሌኮም መሰረተ ልማት መውደም እና ለእቅዱ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል ነው ያሉት።

አክለውም አሁን ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 66 ሚሊየን መድረሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡