በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን – አትሌት ደራርቱ ቱሉ

አትሌት ደራርቱ ቱሉ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) ”በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን” ስትል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ገለጸች።

በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ቡድንም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል በማድረግ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፈችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአዲስ አበባ ለተደረገው ደማቅ አቀባበል አመስግናለች።

“ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ፤ መንግስት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በብዙ መልኩ አግዞናል” በማለት የላቀ ምስጋናዋንም አቅርባለች።

ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል መልስ ለተረገው ደማቅ አቀባበል በተለይም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በብዙ መልኩ ላደረጉት እገዛ የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብላለች፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባመጣነው ውጤት እየተደሰትን ለቀጣይ ውጤቶችም መዘጋጀት አለብን ስትል መልእክቷን ማስተላለፏን ኢዜአ ዘግቧል፡፡