የስልጤ ዞን ከአጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጋር በክልል ለመደራጀት ወሰነ

ሐምሌ 24/2014 (ዋልታ) የስልጤ ዞን ምክር ቤት እያካሄደው ባለው 4ተኛ ዙር 22ኛ መደበኛ ጉባኤው አዲሱ የክልል መዋቅር ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ።

የሕዝቡን መብትና ጥቅም ባስከበረ መልኩ ከአጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጋር በክላስተር ለመደራጀት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዓሊ ከድር በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ነው ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው።

ምክር ቤቱ የስልጤ ዞን ከሀዲያ፣ ጉራጌ፣ ሀላባ እና ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች እንዲሁም ከየም ልዩ ወረዳ ጋር በጋራ ክልል እንዲመሰርት በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።

የአዲሱ ክልል ስያሜና መቀመጫን በተመለከተ በቀጣይ በጋራ ውይይት እንደሚወሰን ደሬቴድ ዘግቧል።