ወልዲያ ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማነት ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 25/2014 (ዋልታ) ወልዲያ ከተማ ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማነት ደረጃ ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርኃ ግብር በከተማዋ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ፒኤችዲ) እና የብልፅግና ፓርቲ አማራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከወልዲያ ከተማ ሕዝብ ጋር ታድመውበታል።

ሬጂዮፖሊስ ለሀገራቸው ከፍተኛ ተግባራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ከተሞች መገለጫ ሲሆን መጠኑ በሀገር ደረጃ ትልቁ ከተማ ሳይሆን በብሔራዊ ሁኔታ ውስጥ አስፈላጊ የሆነ፣ ጥሩ ተደራሽነት ከተሟላ መሠረተ ልማት ጋር አጣምሮ የያዘ፣ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው እና መሰል ባህሪያት በዋነኝነት ከተሞች ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማነት እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል፡፡

በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ሀብትና አቅምን ለመጠቀም እና የበለጠ ለማዳበር ሪጂዮፖሊስ በንግድ አጋሮች እና በቅርብ የከተማ አካባቢዎች መካከል ትስስርን ይፈጥራል፡፡

የወልዲያ ከተማ ለ5 ወራት በአሸባሪው ሕወሓት ቁጥጥር ሥር ሆና በርካታ ግፍ ያስተናገደች ከተማ መሆኗን ኢብኮ በዘገባው አስታውሷል።

በመሆኑም በዚህ ችግር ውስጥ እና አሸባሪው ድል ከሆነ በኋላ በዞኑ በ2014 በጀት ዓመት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ የተሻለ አፈፃፀም ለፈፀሙ ወረዳዎች፣ ከተሞች፣ ለዞን ሴክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያ እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW