ክፍለ ጦሩ የአሸባሪው ሸኔን ታጣቂዎች እየተከታተለ በመደምሰስ ላይ መሆኑ ተገለጸ

ሐምሌ 25/2014 (ዋልታ) በቄለም ወለጋ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ የማያደግም እርምጃ እየወሰደ ያለው ክፍለ ጦር የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎችን እግር በእግር እየተከታተለ መደምሰስ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡
የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ በሕዝባችን ደጀንንነት አሸባሪውን ሸኔ በማያዳግም ሁኔታ የምናጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ ገልፀዋል።
አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የመደምሰስ እርምጃ መወሰዱን ኃላፊው ማስታወቃቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል።
የሬጅመንቱ ዘመቻ ኃላፊ በበኩላቸው ሰራዊታችን ንፁሃንን ካለርህራሄ የሚጨፈጭፈውን ቡድን ለማጥፋት ትጥቁ ሳይላላ፣ ጉልበቱ ሳይዝል፣ በሞራል እና ወኔ በመንቀሳቀስ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ ከማድረግ በተጨማሪ በየጫካው ስንቅ እና ትጥቅ ሲያጓጉዝባቸው የነበሩት የሞተር ሣይክሎች እና የጋማ እንሰሳቶችን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል።