ኢንተርፕራይዙ በ2014 በጀት ዓመት ከ148 ሺሕ በላይ ሰዎች የስራ እድል ፈጠረ

ሐምሌ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአምራች ኢንተርፕራይዝ በ2014 በጀት ዓመት ለ148 ሺሕ 494 ሰዎች የስራ እድል እንደተፈጠረ አስታወቀ።

እያንዳንዱ አምራች የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ ስልጠና እንደተሰጠ ያስታወቀው ተቋሙ ዜጎች የሀገራቸውን ምርት እንዲጠቀሙ ማድረጉንም ነው ያስታወቀው።

በ2014 በጀት ዓመት 2 ሺሕ 761 አዲስ ኢንተርፕራይዞች መፈጠራቸውንም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ተቋሙ በ2014 ወደ ውጪ ከተላከ ምርት ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን የተቋም ምክትል ኃላፊ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ባለፈው በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር ከመፍጠር አንፃር በርካታ ስራዎች መስራቱንም ነው ያስታወቀው።

በ2015 በጀት ዓመት በዋናነት በኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ ምርታማነትን ለማሳደግ ይሰራል ብሏል።

የኢንዱስትሪውን ምርታማነት በ2015 በጀት ዓመት ወደ 65 በመቶ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

በ2015 በጀት ዓመት 4ሺሕ 62 አዲስ ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

የኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለመስጠት እቅድ መያዙን ተቋሙ አስታውቋል።

የመስሪያ ቦታ ችግሮችና የተዘጉ ኢንተርፕራይዞችን ለመክፈት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ተብሏል።

በሱራፌል መንግስቴ