በመዲናዋ በ320 ሚሊዮን ብር የተገነቡ ሶስት የፖሊስ መምሪያዎች ተመረቁ

ነሐሴ 4/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሶስት ክፍለ ከተሞች በ320 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባቸው የፖሊስ መምሪያዎች በዛሬው እለት አስመርቋል::

አዲስ አበባ የበርካታ ዓለም አቀፍ ክንውኖች መዳረሻ እንዲሁም የአፍሪካ መዲና በመሆኗ የፀጥታ ኃይሉን አቅም በማደራጀት በከተማዋ የተረጋጋ የፀጥታ ከባቢን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህም ፖሊስ ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥበት ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል::

ከዚህ አኳያም በ320 ሚሊዮን ብር ወጪ በአራዳ፣ ልደታ እንዲሁም ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የተገነቡት የፖሊስ ጣቢያዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል ብለዋል::

በሔብሮን ዋልታው