የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ

ነሐሴ 12/2014 (ዋልታ) በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የህንድ የአይ.ሲ.ቲ ዘርፍ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ የሚያስችል ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በህንድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ እና የህንድ ኢኮኖሚ ንግድ ድርጅት ጋር በመተባበር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ የህንድ ኩባንያዎችን ለመሳብ ያለመ የበይነ መረብ ኮንፈረንስ አቅርቧል።

በሕንድ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ የመንግሥትን ድጋፍና ማሻሻያ፣ ያለውን ትብብር፣ የመንግሥት ዝግጁነት እና የኢንቨስትመንት አስፈፃሚዎችን አፅንዖት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል መንግሥት በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።

በኮንፈረንሱ ለዘርፉ ነባር የኢንቨስትመንት ድጋፎች፣ የአይሲቲ ፓርክ እድሎች፣ ሀገራዊ መሠረተ ልማት ለባለሀብቶች ቀርበዋል።

በውይይቱ ከባንጋሎር፣ ሃይደራባድ፣ ሙምባይ እና ካሽሚር የቴክኖሎጅ ማዕከላት የተለያየ ደረጃ ያላቸው የአይ.ሲ.ቲ ዘርፍ ኩባንያዎች የየራሳቸውን ፍላጎት እና የምርት ስፔሻላይዜሽን ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW