በአዲስ አበባ በአንድ ጀንበር 4 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርኃ ግብር ተጀመረ

ከንቲባ አዳነች አበቤ

ነሐሴ 12/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጀንበር 4 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርኃ ግብርን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አበቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መንገድ ተገኝተው አስጀምረዋል።

በወቅቱ ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ከተማ 7.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ከእጥፍ በላይ ማሳካት አለብን በማለት ተነስተን 15.5 ሚሊየን ችግኝ በመትከል ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ለዚህም የከተማውን ነዋሪ ያመሰገኑት ከንቲባዋ ችግኞቹ እየተተከሉ ያሉት አስፈላጊና ጠቃሚ በሆኑ ቦታዎች እንደሆኑና በአዲስ አበባ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየተከሰተ ያለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል በሚያግዝ መልኩ እየተተከለ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የሚያለያዩ ችግሮችን እየነቀልን፣ ችግኞችን እየተከልን፣ አብሮነትን እያጠናከርን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አብርሀም በላይን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW