ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ተሽከርካሪዎችን በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት ተጀመረ

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ተሽከርካሪዎችን ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት አስጀመረ።
የተጀመረው አገልግሎት በአንድ ጊዜ 240 መኪኖችን ማጓጓዝ የሚያስችል ሲሆን በዛሬው የማስጀመሪያ መርሐ-ግብር 24 መኪኖችን አጓጉዞ አዲስ አበባ ደርሳል።
ማኅበሩ ዛሬ ያስጀመረው አገልግሎት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋት ከያዘው እቅድ ውስጥ አንዱ ሲሆን በቀጣይ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችን ያስጀምራል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።