ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መመደቡ ተገለጸ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በመመደብ እየሠራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገልጿል።

የአደጋ ጊዜ ምላሽ ማስጀመሪያ መርሀግብር በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስቴሩ ከሳዑዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ የሚገኙ 102 ሺሕ ዜጎችንና በሀገር ውስጥ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ 605 ሺሕ 300 ዜጎችን ለመደገፍ መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው።

በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ተጋላጭ ዜጎች ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረጉም ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢብኮ ነው።