በኦጋዴን መውጣት የሚችል ሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ በጥናት ተረጋገጠ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) የማዕድን ሚኒስቴር አዲስ ባስጠናው ጥናት በኦጋዴን አካባቢ 7 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ መውጣት የሚችል የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩን ማረጋገጡን አስታውቋል።

የነዳጅና የተፈጥሮ ሀብት አቅምና አዋጭነት በተመለከተ የማዕድን ሚኒስቴር የአሜሪካ ኩባንያ ከሆነው ኤልሲኤአይ (LCAI) ጋር የጥናትና እና ሰርተፍኬት ርክክብ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ለአራት ወራት በተካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የሚገኙ የነዳጅ ሀብት መጠን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ርክክብ የተካሄደ ሲሆን የአሜሪካ ኩባንያ በሆነው ኤልሲኤአይ (LCAI) አሸንፎ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ኢምባሲ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ “እስከ ዛሬ አለ እየተባለ በአባቶቻችን ሲነገረን የቆየውን የተፈጥሮ ጋዝ ሀብታችንን እና የወደፊት እጣ ፋንታችንን የሚወስን አንዱ የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋልታ እንዲሆን እንሠራለን” ብለዋል።

የተፈጥሮ ጋዝ ለሀገር ምርት እና ለውጭ ንግድ የምንጠቀምበት ይሆናል ያሉት ሚኒስትሩ ሰርተፍኬቱ ምን ያክል የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለን የምናውቅበት ይሆናል ብለዋል።

የሰርተፍኬቱ ሚና ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ እውቀት ልምድና ፍላጎት ሳይኖራቸው አንቀው የቆዩትን በመላቀቅ ሊሰሩና ሊያለሙ የሚችሉ ትላልቅ ኩባንያዎች ጋር ለመሥራት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን የኢብኮ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW