ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከአሜሪካን አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብፕን ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን እንዳሉት በትምህርት፣ በጤና፣ በቱሪዝም እና በሌሎች የልማት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በተለይም ቱሪዝምን ከማጎልበት እና በቅርስ ጥበቃ ላይ የክልሉ መንግስት በሚያከናውናቸው ተግባራት የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)