ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአልጀርስ የሚገኘውን ሳይዳል የመድኃኒት ፋብርካ ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ነሐሴ 23/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀርስ የሚገኘውን ሳይዳል የመድኃኒት ፋብሪካን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ከትናንት ጀምሮ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በዛሬው ዕለትም በሀገሪቱ ዋና ከተማ የሚገኘውን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ከተመሰረተ 40 ዓመታትን ያስቆጠረው ፋብሪካው 200 የመድኃኒት ዓይነቶችን በማምረት ላይ የሚገኝና በአፍሪካም በግዙፍነቱ የሚጠቀስ ነው።

አፍሪካን በመድኃኒት የማስተሳሰር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም የፋብሪካው አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸውላቸዋል።

በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ መድኃኒት መላክ እንደሚጀምር መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀሪያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በርእሰ መዲናዋ አልጀርስ የሚገኘውን የሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየምን በመጎብኘት በስፍራው የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአልጀሪያ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል መጅድ ታቡኔ ጋር በመገናኘት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በሚጠናከርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW