ሕወሓት በአፍሪካ ሕብረት ወደሚመራው የሰላም ድርድር እንዲመጣ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ተጠየቀ

ነሐሴ 23/2014 (ዋልታ) ሕወሓት በአፍሪካ ሕብረት ወደሚመራው የሰላም ድርድር እንዲመጣ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ በአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት ጠየቀ፡፡

ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ሕወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም ግፊት ማድረግ ይገባዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለሰላም ስምምነት ያለማቋረጥ ጥሪ ያደርጋል ሲልም ጽሕፈት ቤቱ በትውተር ገጹ አስፍሯል፡፡

ይሁን እንጂ ሕወሓት ሌላ ግጭት ለመፍጠር በመምረጥ ወደ ጦርነት መግባቱን በመልዕክቱ ጠቁሟል፡፡