ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን አስረከቡ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የበጎ ፈቃድ ቀንን በማስመልከት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቧሬ አካባቢ ለአቅመ ደካሞችና በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የአቧሬ አካባቢ ነዋሪዎች የተሠሩላቸውን ቤቶች አስረክበዋል።

ይህ ርክክብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጀመረው የዓመታዊ የቤት እድሳት አንድ አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።