“ኢትዮጵያ ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ” – ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) በሰቆጣ ግንባር የአሸባሪውን የህወሓት ታጣቂ ጥቃት ለመከላከል ከተሠለፉ የሠራዊት አባላት መካከል አንዷ ናት ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ።

ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ኢትዮጵያን ተላላኪ የሽብር ቡድን ሰላሟን እንዳያደፈረስ ላፍታም ቢሆን ሳልዘናጋ የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ ብላለች።

አባቶች በመስዋትነታቸው ያስረከቡንን ሀገር በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም ያለች ሲሆን በተሰለፍኩበት ግንባር የሀገሬን ጠላት እስከ መስዋዕትነት ከፍዬ ግዳጄን በቁርጠኝነት እወጣለሁ ነው ያለችው። መረጃው የመከላከያ ሠራዊት ነው፡፡