በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሚገኙ አምራች ኢንድስትሪዎች በመጐብኘት ላይ ናቸዉ

ጳጉሜ 2/2014 (ዋልታ) በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ጳጉሜ 2 ቀን የሚከበረውን የአምራቶች ቀንን ምክኒያት በማደረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሚገኙ አምራች ኢንድስትሪዎችን በመጐብኘት ላይ ናቸዉ።

በጉብኝቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ስራ አስኪያጁ ኢትዮጲያ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ለመተካት በትኩረት እየሰራችባቸው ከምትገኙ ዘርፎች አንዱ የጨረቃ ጨርቅ ውጤት ዘርፉ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ምርት በመጠቀም የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በሜሮን መስፍን