ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቂርቆስ፤ ልደታና አራዳ አረጋዊያን፣ ጡረተኞችና ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው ማዕድ ያጋሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእንግዶቹ መልካም በዓልም መመኘታቸውን የጠ/ሚ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።