አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን የሰላምና የልማት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው – ሙሳ ፋቂ ማህማት

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) “አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን የሰላምና የልማት ዓመት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው” ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ገለጹ።
“ለኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶቼ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ” ሲሉ ሙሳ ፋቂ ማህመት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት የመልካም ምኞት ገልጸዋል።
አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን የሰላም፣ ቁስላቸው የሚሽርበት፣ የእርቅና የልማት እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል።
በተያያዘም ሙሳ ፋቂ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ የስልጣን ጊዜ ማራዘማቸውን አመልክተዋል።
ሊቀ-መንበሩ ከልዑኩ ጋር ባደረጉት ውይይት “በአባሳንጆ ላይ ሙሉ እምነት አለኝ” ያሉ ሲሆን ከ”ሁለቱ ወገኖችና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ” ጋር በኢትዮጵያና በቀጣናው ሰላምና እርቅ እንደሚመጣ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ አድርገው የሾሙት በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም እንደነበር የሚታወስ ነው።