ምርኮኞቹ በህወሓት መሪዎች ምክንያት በርካታ የትግራይ ክልል ልጆች እያለቁ ነው አሉ

መስከረም 3/2015 (ዋልታ) በአሸባሪው ህወሓት መሪዎች ምክንያት በርካታ የትግራይ ክልል ልጆች እያለቁ ነው መሆኑን የምዕራብ ግንባር አዲስ ምርኮኞች ተናገሩ፡፡

አሸባሪው ህወሓት ወደ ጦርነት ማግዷቸው በጥምር ጦሩ የተማረኩ የትግራይ ክልል ወጣቶች ስለ አስከፊው ጦርነት እና ከተማረኩ በኋላ የተደረገላቸውን እንክብካቤ ገልጸዋል።

ለቤተሰቧ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው አፀደ ወልደ ሚካኤል፣ በግዳጅ ወደ ጦርነት መግቧቷን እና በየጦር አውድማው በርካታ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማለቃቸውን ተናግራለች።

ሌላኛው፣ የ16 አመቷ መርሀዊት ግደይ ስልጠና ወስዳ መግባቷን ገልፃ በነበረው ጦርነት አስቸጋሪ ጊዜያትን አሳልፋለች።

ከተማረኩ በኋላ ውጊያው አስከፊ መሆኑን የሚገልፁት ምርኮኞቹ፣ የጁንታው አመራሮች ለራሳቸው ስልጣን እንጂ ለትግራይ ልጆች እያሰቡ አይደለም፤ ጦርነት ይብቃ ሰላም ይሻላል ብለዋል።

በጦርነት እየተሳተፉ የሚገኙ የጁንታው ፕሮፖጋንዳ ሰለባዎች እጃችሁን ለመከላከል ሰራዊት ስጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ እንክብካቤ በማድረግ ላይ መሆኑን የገለፁት ምርከኞቹ፣  በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው ምርኮኞች ወደ ባህርዳር እና አዲስ አበባ ለተሻለ የህክምና ክትትል ተልከዋል ተብሏል።