መስከረም 4/2015 (ዋልታ) አሸባሪውና ወራሪው የሕወሀት ቡድን ለሦስተኛ ጊዜ የከፈተውን ወረራ ለመመከት በሚደረገው ርብርብ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በማይጠብሪ ተከዜ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ጦር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸውን የስንቅ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የግንባሩ የሎጀስቲክ ጠቅላላ ሰብሳቢ የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የመሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ደብረወርቅ ይግዛው አሸባሪው ሕወሓት እንዳሰበው ሳይሆን ሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች መስዋዕት ለመክፈል በጋራ የቆሙበትና ለጥምር ጦሩ ደጀን በመሆን ባንዳውን ቡድን አንገት ያስደፉበት አንድነት ተፈጥሯል ብለዋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለግንባሩ ድጋፍ ማድረጉ አንድነትን የሚያጠናክር እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡
ዩኒቨርሲቲው ግምቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚሆን የፍራሽ፣ የአልጋ፣ የብርድ ልብስ፣ የአንሶላ፣ የጤፍ ዱቄት፣ የሩዝ፣ የመድኃኒትና የተለያዩ ቁሳቁስን ድጋፍ እንዳደረገ ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ጠቁሟል፡፡