ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መተላለፉ ተገለጸ

የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ

መስከረም 4/2015 (ዋልታ) በ2014 በጀት ዓመት ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መተላለፉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ።

የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት 34.69 ቢሊዮን የጋራ ገቢ እና 6.325 ቢሊዮን የውክልና ታክሶችን በመሰብሰብ በጥቅሉ 41.02 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ማስተላለፉን ገልጸዋል።

የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ዘርፍ ተቋማት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ የጋራ ውይይት መድረክ ላይ የተገኙት ሚኒስትሯ በ2014 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 497.45 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 481.71 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አውስተዋል።

በ2015 በጀት ዓመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ 646.75 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡