ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ገቡ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ ከተማ ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ አቀባበል ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።