አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ስለሺ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር እንዲሁም በኢትዮጵያ የስንዴ ልማት እያስገኘ ያለውን ውጤት እና በሌሎች ስኬታም የልማት ስራዎች ላይ ለዋና ዳይሬክተሯ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢንገር አንደርሰን በበኩላቸው በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ፕሮግራም ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ እያከናወነቻቸው በሚገኙ ስራዎች እና በሌሎች የልማት ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW