ሚኒስትሩ በማዕድን ዘርፉ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር መደረጉን ገለጹ

መስከረም 6/2015 (ዋልታ) የማዕድን ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ የአዋጅ ማስተካከያና ፓሊሲ ማሻሻያ ወጥቶለት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር መደረጉን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ተናገሩ፡፡

የማዕድን ዘርፉ ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ በኢንዱስትሪው እና ሌሎች ዘርፎች ግብዓቶችን የማደራጀት ስራ እንደተሰራም ነው የገለፁት።

የማዕድን ሚኒስቴር ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት ዘርፉ ላይ ያሉ ሀብቶችን በመለየት ምርታማነት የማሳደግ እና ኢትዮጵያዊያን ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባቸውን የማዕድን ምርቶች በሀገር ውስጥ የመተካት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እምቅ የማዕድን ሀብት ቢኖራትም ላለፉት አስርት ዓመታት ዘርፉ በተቀናጀ አዋጅና ፓሊሲ ባለመመራቱ ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ ይነገራል።

በሱራፌል መንግስቴ