ም/ጠ/ሚ ደመቀ ህንድ ለኢትዮጵያ ላሳየችው ድጋፍ አመሰገኑ

መስከረም 10/2015 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ህንድ በአስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያ ላሳየችው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማኒያም ጃይሸንከር ጋር ከ77ኛው የተባበሩር መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በዚህም ህንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያሳየቸውን ገለልተኛ እና መርህን የተከተለ አቋም ኢትዮጵያ ታደንቃለች ብለዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ስለከፈተው ጥቃት እና መንግስት በሰሜኑ ያለውን ቀውስ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።