በዳግሚዊት ሞገስ የተመራ ልዑክ ሰመራ ገባ

መስከረም 12/2015 (ዋልታ) በኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግሚዊት ሞገስ የተመራ ልዑክ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ በርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና በሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ልዑካኑ በሰመራ ቆይታው በሎጅስቲክስና ትራንስፖርት ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW