መስከረም 14/2015 (ዋልታ) የበዓል ገበያን የማረጋጋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በበዓላት ወቅት የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በርከት ያሉ ምርቶች ወደ ከተማዋ እንዲገቡ መደረጉን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል።
ምርቶቹ በእሁድ ገበያና በሸማቾች ማህበር እንዲቀርቡ የማድረግና ገበያውን የማረጋጋት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።