መስከረም 17/2015 (ዋልታ) የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ ስርአት መከበሩ ይታወሳል።
በተለይም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምዕመናን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።