የእሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው – ጥራቱ በየነ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያዊያን መገለጫ የሆነው የእሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር በከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ፣ በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አለማየሁ እጅጉ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እና ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማዋ አመራሮች የእሬቻ በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅትን በእሬቻ ፓርክ ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ የማክበሪያ ቦታዎችን የማፅዳት፣ ባህሉን በሚገልፅ መልኩ የማስዋብና ጥበቃ የማድረግ ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የዚሁ ተግባር አንዱ አካል የሆነውን የእሬቻ ፓርክ ባህሉን በሚገልፅ መልኩ የማስዋብና አስፈላጊውን ግብዓት የማሟላት ስራም እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW