ማዲንጎ ራሱን ለሀገሩ የሰጠ ለትውልዱትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መስከረም 19/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ማዲንጎ ራሱን ለሀገሩ የሰጠ፤ ለትውልዱ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ነው” ሲሉ ገለጹ፡፡

ከንቲባ በማዲንጎ አፈወርቅ የአስከሬን ሽኝት ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት “ማዲንጎ  በስጋ ቢለየንም በስራው ህያው ነው“ ብለዋል፡፡

የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎን  ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃፊዎች በአስክሬን ሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

የአርቲስት ማዲንጎ አጭር የስራና የህይወት ታሪክ የቀረበ ሲሆን የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው “ለህብረብሔራዊ አንድነት፣ ለፖን አፍሪካኒዝም ያቀነቀ እና ታሪክ የሰራ ነው“ ብለዋል።

የሀገር መከላከያ  ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነም ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ  ለሀገር ጥሪ ምላሽ መስጠቱንና ሰራዊቱን የጦር ቀጠና በመሄድ ማነቃቃቱን ገልፀው ለቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ድምፃዊ ዳዊት ይፍሩ የድምፃዊው ስራና ልዮ ሙያዊ ችሎታ ሲሆን የአርቲስቱ ልጅ ዲቦራ ማዲንጎም የስንብት ንግግር አድርጋለች።

አንጋፋው አርቲስት መሀሙድ አህሙድን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ አርቲስቶች በማዲንጎ  ህልፈት የተሠማቸውን መሪር ሀዘን ገልፀዋል።

በብሩክታይት አፈሩ