አምባሳደር ስለሽ በቀለ በሎስ አንጀለስ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ስለሽ በቀለ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሲለሺ በቀለ (ዶ/ር) በሎስ አንጀለስ ከኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ባለሀብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ስለሽ ከሎስ አንጀለስ ከተማ የምክር ቤት አባላት ጋር ተገናኝተው ገለፃ ማድረጋቸውን እና ከከተማዋ ከንቲባ ሆን ኤሪክ ጋርሴቲ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ አካባቢ ከቢዝነስ አመራሮችና ባለሀብቶች ጋር ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸውን የጠቀሱት አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ባሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች በማኑፋክቸሪንግ፣ አይቲ፣ ግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና የፋይናንስ ዘርፎች ላይ ጠቃሚ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ኢምባሲ የቆንስላ አገልግሎት ተግዳሮቶች እና ማሻሻያዎች ላይ እና ከማህበረሰቡ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ በአካል እና በዌቢናር መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የዝግጅቱ ተሳታፊዎች በግጭት እና በድርቅ ምክንያት ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን 65 ሺሕ ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!