የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ እና ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ የራሱን ሚና መጫወት እንደሚገባ ተገለጸ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ እና ለማረጋገጥ መንግስት በትኩረት እየሰራ ቢሆንም የግሉ ዘርፍ የራሱን ሚና መጫወት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የሳይበር ደኅንነት የአገራችን ሉአላዊነት ማረጋገጥ የሚቻልበት አንዱ መንገድ በመሆኑ ትኩረት እይደሚፈልግ ገልጸው ዘርፉን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ታዳጊዎችና ወጣቶች ላይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሳይበር ዲፖሎማሲን ማሳደጊያ ሌላ መንገድ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚም ሁሉም የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን መፈተሽና ማዘመን ይገባል ብለዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር ዋና የዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው የሳይበር ደህንነት ወር በዋናነት ዓለም በዘርፉ የደረሰበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም የኢንፎርሜሽን የበላይነትና ብሄራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የቴክኖሎጅና እውቀት ባለቤትነት፣ ወሳኝ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ትብብርና ቅንጅት እንዲሁም ተቋማዊ ልህቀት ላይ በተለየ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የሳይበር ደህንነት ወር በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

በህይወት አክሊሉ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW