በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ከ303 ሺሕ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት አስተባባሪነት መንግስት ያቀረበውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ከ303 ሺሕ ዶላር በላይ ተሰብስቧል።

ከድጋፉ ውስጥ 300 ሺሕ የሚሆነው ከዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማኅበር የተዋጣ ሲሆን፣ ዲፕሎማቶችና ግለሰቦችም ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

መንግስት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በልዩ ልዩ ሀገራት የሚገኙ የኢፌዴሪ ሚሲዮኖች የሀብት ማሰባሰብ ስራዎችን አጠናክረው መቀጠላቸው ተጠቅሷል።

ከዚህ በፊት በአቡዳቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከዳያስፖራው ከ560 ሺሕ ዶላር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።