22ኛው የዓለም የእይታ ቀን በሀረር ከተማ ተከበረ

ዶ/ር ደረጀ ድጉማ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) 22ኛው የዓለም የእይታ ቀን “ትኩረት ለዓይናችን” በሚል መሪ ቃል በሀረር ከተማ ተከብሯል።

እለቱን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ለዓይን ህክምና የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ትኩረት በመስጠት በሁሉም የጤና ተቋማት የዓይን ጤና ህክምና አገልግሎት ለማስፋፋት ይሰራል ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላትም ለዓይን ህክምና ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ እና የባህልና ስፖርት ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው (ዶ/ር) የዓይን ህክም አገልግሎት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጥ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ይከናወናል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን አብዱላሂ በበኩላቸው የእይታ ችግር በሁለተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለው አመላክተው የእይታ ቀን መከበሩም በህክማና ማስቀረት የሚቻልን ዓይነ-ስውርነትን ለመከላከል ያስችላል ነው ያሉት።

ከሀገሪቱ ዜጎች 1 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ዓይነ-ስውራን ሲሆን 3 ነጥብ 6 በመቶው የሚሆነው ዜጋ ደግሞ የዓይን እክል እንዳለበት ተጠቁሟል።

በእለቱም በከተማው በስድስት የተለያዩ አካባቢዎች የዓይን ምርመራ እየተደረገ ሲሆን ምርመራውም ለቀጣይ አንድ ወር እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW