ከኢትዮጵያ 16 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዞ የወጣው ህንዳዊ በቁጥጥር ስር ዋለ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) ከኢትዮጵያ 16 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዞ የወጣው ህንዳዊ በህንድ ሙምባይ አየር ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ሙምባይ የተጓዘ ህንዳዊ 16 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉን የህንድ ጉምሩክ ባለስላጣን አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች የኮንትሮባንድ ወርቅን ለመደበቅ ቢሞክሩም የጉምሩክ ክፍሉ ባገኘው ልዩ መረጃ መሰረት መያዝ መቻሉን ጠቁሟል፡፡